Sunday, November 24, 2024
spot_img

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ታግተው የነበሩ 11 ኢትዮጵያዊያንን ከእገታ ማስለቀቁ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ጥቅምት 14፣ 2014 ― የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በጆሃንስበርግ ታግተው የነበሩ 11 ኢትዮጵያዊያንን ከእገታ ማስለቀቁ ተነግሯል።

ፖሊስ አስለቅቋቸዋል ከተባሉት መካከል አምስቱ ሰዎች የታገቱት ዌስተርን ኬፕ ከተባለ አውራጃ መሆኑ ነው የተሰማው።

በሌላ በኩል ፖሊስ ከትላንት በስትያ ሁለት ተጠርጣሪ አጋቾችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ መናገሩን የተገለጸ ሲሆን፣ ተጠርጣሪዎቹ ታጋቾቹ የታገቱበትን መጋዘን ሲጠብቁ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው ተብሏል።

የአጋቾች ዓላማ የእገተ ገንዘብ መጠየቅ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል። በርካታ ኢትዮጵያውያን ለሥራ በሚያቀኑባት ደቡብ አፍሪካ በቅርብ ጊዜያት ሰዎችን እያገቱ ገንዘብ መጠየቅ እየተለመደ መምጣቱን አምባ ዲጂታል በአገሩ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰምቷል።

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት 50 ኢትዮጵያውያንን በማገትና በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠረ ግለሰብ ፍርድ ቤት መቅረቡ ተነግሮ ነበር።

የ50 ዓመቱ አሕመድ ካፌቾ ባለፈው ሳምንት ከ 12 እስከ 50 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 50 ኢትዮጵያውያንን ያገተው ዘካሪያ በተባለ መናፈሻ ውስጥ ነበር። ግለሰቡ አጋቾቹን ታጋቾቹ እንዲለቀቁ ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ በመጠየቅ ወንጀል ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው።

የአገሪቱ ብሔራዊ ዓቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ከእገታው የተረፉት ሰዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዴት እንደገቡና በአገሪቱ ውስጥ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ከሀገር ውስጥ ጉዳይ መምሪያ ጋር እየሰራ መሆኑን መግለጹም ተነግሯል።

ደቡብ አፍሪካ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሕገ ወጥ መንገድ የሚጓዙባት መሆኗ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img