Sunday, October 13, 2024
spot_img

አቶ ሙስጠፋ መሐመድ ዳግም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተደርገው ተመረጡ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 8፣ 2014 ― መስከረም 20፣ 2014 በሶማሌ ክልል የተካሄደውን 6ኛው አገር ዐቀፍ ምርጫ ተከትሎ በክልሉ ርዕሰ ከተማ ጅግጅጋ ከተማ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት በዛሬው እለት የመንግስት ምሥረታ አድርጓል፡፡

263 መቀመጫዎች ያለው የክልሉ የምክር ቤት መስራች ጉባኤ፣ የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ መርጧል፡፡ በዚሁ መሠረት አያን አብዲን አፈ ጉባኤ አድርጎ የሰየመው ምክር ቤቱ፣ አቶ ኢብራሂም ሐሰንን ምክትል አፈ-ጉባኤ አድርጓል፡፡

ምክር ቤቱ በክልሉ ምርጫ ያሸነፈው ብልፅግና ፓርቲ ያቀረባቸውን ባለፉት ሦስት ዓመታት ክልሉን የመሩትን አቶ ሙስጠፋ መሐመድን ዕጩ ተደርገው የቀረቡትን በርዕሰ መስተዳድርነት መርጧል፡፡ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የክልሉ አቶ ኢብራሂም ኡስማንን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img