Sunday, October 6, 2024
spot_img

የአብኑ ጣሂር መሐመድ የአማራ ቱሪዝም ቢሮን እንዲመሩ ተሾሙ

ምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 20፣ 2014 ― የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጣሂር መሐመድ የአማራ ክልል የቱሪዝም ቢሮን በኃላፊነት እንዲመሩ ተሹመዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት፤ አቶ ጣሂርን ጨምሮ 24 የክልሉ መንግስት ተቋማትን የሚመሩ ኃላፊዎችን ሹመት በዛሬው የምስረታ ጉባኤው አጽቋል።

ምክር ቤቱ ከዚህም በተጨማሪ የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተለያዩ ዘርፎችን የሚያስተባብሩ ሶስት የስራ ኃላፊዎችን ሹመትም አጽድቋል። የአማራ ክልልን በምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት እንዲመሩ የተሾሙት ጌታቸው ጀምበር ናቸው።

የቀድሞው የክልሉ ሰላም እና ህዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪነት ሹመት አግኝተዋል። አቶ ስዩም ተሾመ የማህበራዊ ጉዳዮች ክላስተርነት በአስተባባሪነት እንዲመሩ ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

በፌደራል የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት አይናለም ንጉሴ ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አስተባበሪ ሆነዋል። አይናለም ንጉሴ የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተሾሙት በጥቅምት 2011 ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img