አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 18፣ 2014 ― የፌደራል የመከላከያ እንዲሁም የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሮች የአዲስ አበባ ቢሮዎችን እንዲመሩ በዛሬው እለት ተሹመዋል።
የቀድሞውን ሚኒስቴር አቶ ለማ መገርሳን ተክተው የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾመው የነበሩት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ፤ የአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮን በኃላፊነት እንዲመሩ ሲሾሙ፣ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ደግሞ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ እንዲሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተሹመዋል።