Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሱዳን ጦር እና የሲቪል አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ልዩነት መካረሩ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 17፣ 2014 ― ከቀናት በፊት መፈንቅለ መንግስት ተሞክሮ አክሽፌያለሁ ያለችው ሱዳን በጥምረት በሚመሯት በጦሯ እና በሲቪል አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ልዩነት መካረሩን ያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

ሱዳን የሲቪል አስተዳደሯ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሃምዶክ የሚመራ ሲሆን፣ ጦሩን የሚመሩት ደግሞ ጀነራል ዐብዱልፈታህ አል ቡርሃን መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ቀድሞም በቋፍ ላይ እንደነበር ሲነገር የነበረው በሁለቱ አካላት መካከል ያለው ግንኙነት ባለፈው ሳምንት መፈንቅለ መንግስት ተሞክሯል መባሉን ተከትሎ ልዩነቱ ሰፍቷል ነው የተባለው፡፡

ከሽፏል ከተባለው መፈንቅለ መንግስት በኋላ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው በጦር ኃይሉ የውስጥ እና የውጭ አካላት የተቀናበረ ነው ሲሉ ቢናገሩም፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌ/ጄ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በበኩላቸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን ‹‹ሌላ ማንም ሳይሆን ጦሩ ነው ያመከነው›› ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አሁን ደግሞ ወታደራዊ ምክር ቤቱ ከሲቪል አስተዳደሩ አካል ጋር የሚደረጉ ሁሉንም ስብብባዎች መሰረዙን ሲያስታውቅ፣ በአጸፋው የአገሪቱ የባለሞያዎች ማኅበር የሲቪል አስተዳደሩ ከወታደራዊ ምክር ጋር ያለውን ጥምረት እንዲተው ጥሪ አድርጓል፡፡

ውጥረቱን ተከትሎም በአሁኑ ወቅት በዋና ከተማዋ ካርቱም የሚገኘው ወታደራዊ እዝ በተጠንቀቅ እንዲቆም እንደታዘዘ ነው የተነገረው፡፡

በሱዳን ከሲቪል እና ከጦሩ አመራሮች የተውጣጣው 11 አባላት ያለው ቡድን የተዋቀረው በ2011 መጨረሻ ላይ ነበር፡፡ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት የሚባለው ይህ አካል በ39 ወራት ውስጥ ማለትም እስከ ኅዳር ድረስ ምርጫ አካሂዶ አዲስ መንግስት እንዲመሰረት የማድረግ ሃገራዊ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img