Sunday, October 6, 2024
spot_img

አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የፊታችን ቅዳሜ ይመሠረታል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 13፣ 2014 ― ጨፌ ኦሮሚያ መስከረም 15 በሚካሄደው ጉባኤ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንደሚመሰረት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ገልጸዋል፡፡

አፈ ጉባኤዋ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 15 5ኛው ዙር የጨፌ ኦሮሚያ ማጠቃለያ እና 6ኛው ዙር ጨፌ ኦሮሚያ የመጀመሪያ ጉባኤ ይካሄዳል ብለዋል።

በጉባኤው ነባር የጨፌው አባላት የሚሸኙበትና አዲሶቹ የሚተኩበት እንደሚሆንም አስታውቀዋል፡፡

በጉባኤው አዲሱ የክልሉ ርእሰ መስተዳድርን ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት እንደሚሰየሙ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ 5 አመታት የኦሮሚያ ክልልን የሚመራው አዲስ የክልሉ መንግስት ምስረታው ከመካሄዱ በፊት የጨፌ ኦሮሚያ 2013 ላይ ያልቋጫቸውን እየተጠናቀቁ ያሉ ረቂቅ አዋጆችና አንዳንድ ጉዳዮች አየታዩ መሆኑን የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ነው፡፡

የፎቶ ምንጭ፡ EBC

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img