Sunday, October 6, 2024
spot_img

በትግራይ በረሐብ ሰበብ ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ርሃብ ገብቷል ሲል አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል። በክልሉ አንዳንድ ቦታዎች የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሰዎች ለቀናት ሳር ለመመገብ እንደተገደዱ እና በአንድ ጤና ጣቢያ አንዲት ወላድ እና ጨቅላ ልጇ በዚሁ ረሐብ ሰበብ እንደሞቱ ዘገባው ጠቅሷል።

የመቀሌው ኣይደር ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሐየሎም ከበደ በሆስፒታሉ የጽኑ በሽታ ክፍል ሕክምና ላይ ያሉ እና በምግብ እጥረት ክፉኛ የተጎዱ 50 ሕጻናትን ፎቶ አጋርተውት መመልከቱን የዜና ወኪሉ ጠቅሷል።

በትግራይ ሰዎች እየሞቱ መሆኑን ለጤና ሚኒስቴር ቢያሳውቁም፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንስተላልፋለን መባላቸውን ያስታወሱት ዶክተር ሐየሎም፣ የሚያደርጉት ግራ ቢገባቸው ማልቀሳቸውን መናገራቸውም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ መድሃኒት እየተመናመነ መሆኑን ያስረዱት ዶክተሩ፣ ከሰኔ ወር አንስቶ ለጤና ባለሞያዎች ደመወዝ አለመከፈሉንም ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡

ባለፈው ሳምንት በትግራይ የሚደረገውን የሰብአዊ አቅርቦት በተመለከተ የተናገሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክረታሪ ቢልለኔ ሥዩም፣ በክልሉ ከ6 ሺሕ ቶን በላይ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ከ50 ሺሕ በላይ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ በላይ መቅረቡን በመግለጽ፣ 760 ሺሕ ሊትር ገደማ ነዳጅ እንዲሁም ከ1 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ምርጥ ዘር መቅረቡንም አስታውቀዋል፡፡

ቢልለኔ አክለውም ወደ ክልሉ የሚቀርቡ ሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማቀላጠፍ በሚል የፍተሻ ጣቢያዎችን ቁጥር ወደ 2 መቀነሱንም ገልጸዋል፡፡

ፎቶ፡ በትግራይ በምግብ እጥረት የተጎዳ መሆኑ የተገለፀ ሕፃን

ምንጭ አሶሼትድ ፕረስ

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img