Sunday, October 6, 2024
spot_img

ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ ለፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 10፣ 2014 ― በዓለም የቦክስ ውድድር መድረኮች ኮከብ የሆነው ፊሊፒንሳዊው ማኒ ፓኪዎ በቀጣይ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አድርጓል፡፡

ፓኪዮ ገዢውን ፓርቲ በሚቀናቀነው ፒዲፒ-ላባን ፓርቲ አማካኝነት ነው ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ለምርጫው የሚቀርበው።

በበርካታ ድሎች ከታጀበው ቦክሰኝነቱ ባሻገር የ42 ዓመቱ ፓኪዎ በፊሊፒንስ ፓርላማ ውስጥ ሴናተርም ነው።

በስልጣን ላይ የሚገኙት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ለሌላ የስልጣን ዘመን መወዳደር ባይችሉም አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ዕጩ አድርጎ አቅርቧቸዋል።

ሂደቱን በቅርበት የሚከታተሉ ተቺዎች የዱቴርቴ ተግባር ስልጣንን የሙጥኝ የማለት ሙከራ ሲሉ ትችት እያቀረቡባቸው ይገኛሉ።

ዱቴርቴ ከቅርብ ወዳጃቸው ክሪስቶፈር ቦንግ ጎ ጋር ለምርጫው እንዲቀርቡ የተመረጠ ቢሆንም ክሪስቶፈር ግን ወዳጃቸውን ዱተርቴንን ለመተካት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት የፕሬዚዳንት ዱቴርቴ ሴት ልጅ ሳራ ዱቴርቴ-ካርፒዮ አባቷን ለመተካት ለውድድር ልትቀርብ እንደምትችል ፍንጮች አሉ።

ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ በውድድር ሕይወቱ በስምንት የተለያዩ የክብደት ምድቦች ያሸነፈ ሲሆን፣ በቅርቡም ከኩባዊ ተቀናቃኙ ጋር ባደረገው ግጥሚያ መሸነፉን ተከትሎ ከቦክሱ አለም ራሱን ለማግለል ማሰቡን አስታውቋል።

የቀረበለትን የፕሬዘዳንትነት ጥያቄ በተቀበለበት ግዜም “እኔ ታጋይ ነኝ፤ በግጥሚያ መድረክ (ቦክስ) ሆነም ውጪ ታጋይ ሆኜ ቀጥላለሁ” ብሏል።

በድቡብ ምስራቅ ኢሲያ በምትገኘው ፊሊፒስ እጅግ ዝነኛ የሆነው ፓኪዮ በምርጫው አሸንፎ ስልጣን የሚይዝ ከሆነ ድህነትን እና ሙስናን አዋጋለሁ ሲል ቃል መግባቱን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img