Sunday, October 6, 2024
spot_img

እስራኤል ከእስር ቤት ያመለጡ ሁሉንም ፍልስጤማውያን ይዣለሁ አለች

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 10፣ 2014 ― የእስራኤል ጦር ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ካመለጡት ስድስት ፍልስጥኤማዊ መካከል የመጨረሻዎቹን ሁለቱን በቁጥጥር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

እስራኤል ባለፈው ሳምንት አራቱን እስረኞች የያዘች ሲሆን፣ የተቀሩትን ሁለት እስረኞች በዌስት ባንክ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ከተከበቡ በኋላ ተይዘው ወደ እስር ቤት መወሰዳቸውን ነው የእስራኤል መከላከያ ኃይል ሰራዊት የገለጸው፡፡

በፍልስጥኤማውያን ዘንድ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሮ የነበረው የእስረኞቹ ማምለጥን በተመለከተ ምርመራ እንደተጀመረ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ትላንት እሑድ በዌስት ባንክ የተቀሩትን ሁሉቱን እሰረኞች ለመያዝ በተደረገው እንቅስቃሴ በእስራኤል ኃይሎች እና በፍልስጥኤማውያን ተቃዋሚዎች መካከል ግጭ ተቀስቅሶ የነበረ ቢሆንም እስረኞቹ ግን ያለማንገራገር እጅ መስጠታቸውን የእስራኤል ፖሊስ ገልጿል።

ከእስረኞቹ የአንዱ አባት ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደተናገረው ልጃቸው የሸሸጉትን ‹‹የቤት ባለቤቶች አደጋ ላይ ላለመጣል›› እጁን ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img