Friday, October 18, 2024
spot_img

መኪና አስመጪዎች አዲሱ ፓርላማ ከመምጣቱ በፊት ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 27፣ 2013 ― ከኤክሳይዝ ታክስ ክለሳ ጋር ተያይዞ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ከታክስ ክለሳው በፊት ለመግባት ሂደት የጀመሩ ከሆነ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ በቀድሞው ቀረጥ እንዲገቡ ቢፈቀድም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እክል በማሳደሩ መኪኖቹ በወቅቱ መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል።

ይህን ተከትሎ አዲሱን ኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ያፀደቀው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፍትሄ እንዲያበጅ በማህበራቸው በኩል መጠየቃቸው የተነገረ አስመጪዎች፣ ለአንድ አመት ያክል ምላሽ አላገኘንም በማለት ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

በመሆኑም ዛሬ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አዲሱ ፓርላማ ከመምጣቱ በፊት መፍትሄ ይሰጠን ሲሉ ተማፅኖ አቅርበዋል።

በአስመጪዎቸ ተጭነው በጉምሩክ መጋዘን እና ጅቡቲ አሉ የተባሉ መኪኖች ብዛት 637 መሆኑን የዘገበው ካፒታል ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img