Thursday, October 10, 2024
spot_img

በጣልያኗ ደሴት ከ500 በላይ ስደተኞችን መታደግ እንደተቻለ ተገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― የጣልያን የባሕር ጠረፍ ጠባቂ መርከቦች ላምፔዱዛ ደሴት ላይ እየተንሳፈፈ ካለ የዓሣ ማጥመጃ ጀልባ ላይ 539 ስደተኞችን ማዳናቸውን አስታውቀዋል።

ቅዳሜ ዕለት የተደረገው የማዳን እርዳታ በአንድ ቀን ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ ስደተኞችን ወደ ጣልያኗ ደሴትም ያስገባ ነው ተብሏል።

በጀልባው ውስጥ ከተሳፈሩት ውስጥ ሴቶችና ሕፃናት እንደነበሩበትም የተገለጸ ሲሆን፣ ከሊቢያ በሜድትራኒያን ባህር አቋርጠው ከተጓዙት ስደተኞች መካከል አንዳንዶቹ የነውጠኝነት ባህርይ ታይቶባቸዋል ተብሏል።

የጣልያን ዓቃብያነ ሕግ በአጠቃላይ ሁኔታው ላይ እንዴት ተፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ምርመራ ከፍተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ መርማሪዎቹ ስደተኞቹ በሊቢያ በሐሰት የታሰሩ ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታ እየተመለከቱ መሆኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ስደተኞቹን ወደ ላምፔዱዛ ለማጓጓዝ ሁለት የባህር ዳርቻ ጠባቂ መርከቦች እና የጉምሩክ ጀልባ ከጣሊያን የገንዘብ ወንጀሎች ፖሊስ ጋርዲያ ዲ ፋንዛ ጋር ተጣምረው ተባብረዋል ተብሏል።

የደሴቲቱ ከንቲባ ቶቶ ማርቲሎ የዳኑትን ስደተኞች አስመልክቶ ‹‹ከቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከተፈፀሙ ትላልቅ ስራዎች አንዱ›› ሲሉ አሞካሽተዋል መባሉንም የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ላምፔዱዛ ወደ አውሮፓ ለመድረስ ከሚጓዙ ስደተኞች መካከል በዋናነት የሚረግጧት መዳረሻ ናት።

ደሴቲቱ ከ300 ያነሱ ሰዎችን ለመቀበል የስደተኞች ካምፕ ቢኖራትም በአሁኑ ውስጥ በደሴቲቱ ያለው የስደተኛ ቁጥር ከአምስት እጥፍ በላይ ነው። በርካቶችም አቧራሟ በሆነው መንገድ አካባቢ የሚገኙ ሲሆን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ከሌለው አገራትም እንደሚመጡ ተገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img