Sunday, September 22, 2024
spot_img

ሃገራት ዜጎቻቸው ወደ ካቡል አየር ማረፊያ እንዳይሄዱ አስጠነቀቁ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 20፣ 2013 ― በርካታ ሃገራት በአፍጋኒስታኑ ካቡል አየር ማረፊያ የሽብር ጥቃት ሊኖር ስለሚችል ዜጎቻቸው ወደ አየር ማረፊያ እንዳይሄዱ አስጠንቅቀዋል።

ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያውን ከሰጡት መካከል አውስትራሊያ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ዩናይትድ ኪንግደም ይገኙበታል፡፡

ከአየር ማረፊያው ውጪ ያሉ ሰዎችም አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ ተነግሯቸዋል።

ማስጠንቀቂያውን ከሰጡት መካከል የአውስትራሊያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ‹‹በአሁን ወቅት በጣም አስጊ የሆነ የሽብር ጥቃት አለ›› ሲል አሳውቋል፡፡

ይህ የሽብር ጥቃት ማስጠንቀቂያ የተሰጠው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በካቡል አየር ማረፊያ የምስራቅና ሰሜን መግቢያ ያሉ ሰዎች ሥፍራውን እንዲለቁ ካሳሰበች በኋላ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ዩናይትድ ኪንግደምም በተመሳሳይ ‘በሥፍራው ያሉ ሰዎች ደኅንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ ሄደው ሁኔታውን ይከታተሉ’ ብላለች።

ከ10 ቀናት በፊት በታሊባን ታጣቂዎች እጅ ሥር በወደቀው ካቡል አየር ማረፊያ በኩል ከ82 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከአፍጋኒስታን ወጥተዋል የተባለ ሲሆን፣ የተለያዩ ሃገራት ከተቀመጠላቸው የነሃሴ 25 ቀነ ገደብ በፊት ዜጎቻቸውን ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት እየተሯሯጡ እንደሚገኙም ነው የተነገረው፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም አየር ማረፊያ ውስጥና ውጪ ተኮልኩለው አፍጋኒስታንን ጥለው ለመውጣት እየተጠባበቁ እንደሚገኙም ዘገባው አክሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img