Monday, September 23, 2024
spot_img

ሲአይኤ እና ታሊባን በምስጢር መወያየታቸው ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 19፣ 2013 ― የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲአይኤ ዋና ኃላፊ በምስጢር ከታሊባን መሪ ጋር ሰኞ ዕለት ካቡል ውስጥ መገናኘታቸውን አንዳንድ ምንጮች ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን መናገራቸው ተገልጧል፡፡

ሆኖም በዊሊያም በርንስ እና ሙላህ ባራዳር መካከል ውይይት ስለመደረጉ የሚያረጋግጥ ነገር ከሁለቱም በኩል እስካሁን አልተነገረም።

ኒውዮርክ ታይምስ፣ ዘ ዋሽንግተን ፖስት፣ አሶሺዬትድ ፕረስ እና ኤንፒአር ያሉ የአሜሪካ የዜና ወኪሎች ከአንዳንድ ምንጮች ሰማን እንዳሉት ሲአይኤ እና ታሊባን በሚስጥር ተገናኝተዋል የተባለ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ በጣም ትንሽ መረጃ ነው በጉዳዩ ላይ የወጣው።

ይህ ዜና መረጋገጥ የሚችል ከሆነ ታሊባን በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና ያለውን የአፍጋኒስታን መንግሥት መሸሽ ተከትሎ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ወዲህ አሜሪካና እና ታሊባን ያደረጉት የመጀመሪያው ግንኙነት ይሆናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት እስከ 5 ሺሕ 800 የሚደርሱ የአሜሪካ ወታደሮች እስካሁን ድረስ በካቡል ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎችንና አገሪቱን ለመልቀቅ የሚፈልጉ አፍጋኒስታናውያንን ጥበቃ እያደረጉላቸው ይገኛል፡፡

ዋሽንግተን ፖስት፤ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገው ውይይት ምናልባት የአሜሪካ ወታደሮች በአውሮፕላን ከአገር የሚያስወጧቸው ዜጎቻቸውን በተመለከተ ስላለው ቀነ ቀደብ ዙሪያ ሊሆን እንደሚችል ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪ ትናንት ማክሰኞ ዕለት ደግሞ ታሊባን ከዚህ በኋላ ማንኛውም አፍጋኒስታናዊ አገሪቱን ለቆ መውጣት እንደማይችል ያስታወቀ ሲሆን፤ አሜሪካ ወታደሮቿን ለማስወጣት ያስቀመጠቸው ቀነ ገደብም እንደማይቀየር ገልጿል።

የታሊባኑ መሪ ሙላህ ባራዳር በአውሮፓውያኑ 1949 ታሊባንን ከመሰረቱት አራት ሰዎች መካከል አንደኛው ናቸው። 2010 ላይ ደግሞ በአሜሪካና ፓኪስታን ጥምረት በመተካሄደ ወታደራዊ ዘመቻ በቁጥጥር ስር ውለው ለስምንት ዓመታት በእስር አሳልፈዋል።

ከ2019 ጀምሮ ሙላህ ባራዳር ኳታር የሚገኘው የታሊባን ፖለቲካዊ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ ኃላፊ ነበሩ። የካቲት 2020 ላይ ደግሞ ዶሃ ውስጥ የአሜሪካ እና የኔቶ ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ስምምነት ፈርመዋል።

ሰውየው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካ መሪ ጋር መነጋገር የቻሉ የታሊባን መሪ ሲሆኑ፣ 2020 ላይ ከወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ ውይይት አድርገዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img