Monday, September 23, 2024
spot_img

እስራኤል በጋዛ የፈጸመችው የአየር ድብደባ የጦር ወንጀል ሊሆን እንደሚችል ሂውማን ራይትስ ዎች አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― ከወራት በፊት በጋዛ ሰርጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አራት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎችን ያፈረሰው የእስራኤል የአየር ድብደባ የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ እንዳለው በጥቃቶቹ የተጎዳ ሰው ባይኖርም በደርዘን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ቤት አልባ ሆነዋል።

እስራኤል ህንጻዎቹን ለመምታት የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድኖች ህንጻዎቹን ለወታደራዊ ዓላማ ተጠቅመዋል ብሎም ሲቪሎችን በከለላነት የሚሉ ምክንያቶችን ማስቀመጧ ይታወሳል። ሂውማን ራይት ዋች ግን እስራኤል እነዚያን ክሶች የሚደግፍ ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረበችም ብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጋዛ ለ 11 ቀናት በቆየው በዚሁ ግጭት ቢያንስ 256 ሰዎች መገደላቸውን እና በእስራኤል ደግሞ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉን መገልጹ አይዘነጋም፡፡

ግጭቱ ለሳምንታት በምስራቅ እየሩሳሌም ከቆየው የእስራኤል-ፍልስጤም ውጥረት በኋላ በሙስሊሞች እና በአይሁዶች ዘንድ ቅዱስ በሆነው ስፍራ ውጥረቱ የፈነዳ ሲሆን፣ ጋዛን የሚቆጣጠረው ታጣቂው እስላማዊ ቡድን ሃማስ እስራኤል ከጣቢያው እንድትወጣ ካስጠነቀቀ በኋላ ሮኬቶችን መተኮስ ጀምሮ ነበር፡፡

ይህም በእስራኤል የአፀፋዊ የአየር ድብደባዎችን አስከትሎ፣ ይህን ተከትሎ እኤአ ከግንቦት 11 እስከ 15 ባለው ጊዜ ውስጥ እስራኤል በጋዛ ከተማ ውስጥ የሚገኙትን የሃንዲ፣ የጃዋራ፣ የሾሮክ እና የጃላ ማማዎችን ያወደመችው።

የሂውማን ራይትስ ሪፖርት እንደሚያሰየው የእስራኤል ጦር በህንጻው ውስጥ ያሉ ሰዎች ጥለው እንዲወጡ እና ድብደባ ሊፈጸም እንደሚችል ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥቷል።

የእስራኤል ባለሥልጣናት የሕንፃዎቹ የተወሰኑ ክፍሎች የሐማስን እና የሌሎች የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖችን ጽሕፈት ቤቶች እንደያዙ ብሎም የአንዳንድ ክንፎች ዋና መስሪያቤት እና የወታደራዊ ስለላ መቀመጫ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋል።

እንዲሁም ከህንጻዎቹ በአንዱ ውስጥ ሃማስ በእስራኤል ላይ የሚጠቀመው «በጣም ዋጋ ያለው የቴክኖሎጂ መሣሪያ» የሚገኝበትን ጽሕፈት ቤትን ያካተተ ነበር ሲሉም ተደምጠዋል።

የሂውማን ራይትስ ዋች ምርመራ ጥቃቱን በተመለከቱ ብሎም በጥቃቱ ምክኒያት ጉዳት በደረሰባቸው 18 ፍልስጤማውያን ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ ላይ ሲሆን የቪዲዮዎች ብሎም የፎቶግራፍ ማስረጃዎች ለጥናቱ ግብአት ሆነዋል መባሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img