አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 17፣ 2013 ― የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ዳግመኛ ሊነሳ የሚታሰብ ብጥብጥ፣ ነውጥ እና ዘረፋን በጭራሽ አልታገስም ሲል አስጠንቅቋል፡፡
የፖሊስ ማስጠንቀቂያ የተሰማው በየማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ፀረ መንግሥት የተቃውሞ ጥሪው ቅብብሎሽ ባየለበት ወቅት እንደሆነ ነው የተሰማው፡፡
ከወር በፊት የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በችሎት መድፈር የዓመት ከ3 ወራት እስር ተፈርዶባቸው ወህኒ መውረዳቸውን የተቃወሙ ደጋፊዎቻቸው ያስነሱት ተቃውሞ አገሪቱን ለነውጥ ዳርጓት መጠነ ሰፊ ዘረፋ እና ውድመት መድረሱ ይታወቃል፡፡
የቀደመው ነውጥ ከ200 ያላነሱ ሰዎች ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን፣ የአዲሱ ተቃውሞ ወሬ መሰማት የያዘው አገሪቱ ከቀዳሚው ነውጥ የዞረ ድምር ሳትላቀቅ እንደሆነ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡