Sunday, October 6, 2024
spot_img

በዳርፉር የነበሩ ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የሆኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በጅቡቲ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን በአገሩ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 17፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አርማ ተደርጎባቸው በአሚሶም ስር በዳርፉር የሰላም ማስከበር ስራ ላይ የነበሩና ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የሆኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በጅቡቲ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን በአገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እወቁት ብሏል፡፡

ኤምባሲው በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው ማስታወሻ እነዚህ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች አርማቸው ተለውጦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትን እንደሚቀላቀሉ ገልጧል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ ስር ኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወታደሮችንና የፖሊስ ኃይል ያሰማራችበት የዳርፉር ሠላም ማስከበር ተልዕኮ በተያዘው ዓመት ጥር ወር መጠናቀቁ ተነግሮ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ስር በተለያዩ አገራት ውስጥ ለሚደረጉ የሠላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ የሚባለውን ከ8 ሺሕ 300 በላይ ሠራዊት የምታበረክት ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር በሱዳን ውስጥ በሚገኙት ዳርፉርና በአብዬ ግዛት ውስጥ የተሰማሩ ነበሩ፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img