Thursday, October 17, 2024
spot_img

ቤተ እስራኤላዊያን ሴቶች በሥራ ቦታ መገለል እንደሚደርስባቸው አንድ ጥናት አመለከተ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 15፣ 2013 ― ከኢትዮጵያ የሄዱ ቤተ እስራኤላዊያን ሴቶች ሥራ ለማግኘት እንደሚቸገሩና በሥራ ቦታቸውም መገለል እንደሚደርስባቸው አድቫ ሴንተር የተባለ አጥኚ ያወጣው ግኝት አመልክቷል፡፡

እነዚሁ ከኢትዮጵያ የሄዱ ሴቶች ይደርስባቸዋል ከተባለው መገለል በተጨማሪ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ እንደሆኑና እድገት ለማግኘት እንደሚቸገሩ ተመላክቷል፡፡

ለገበያው ተፎካካሪ የሚያደርግ ትምህርት እና ሥልጠናዎች የማግኘጥ እድላቸው ስለተገደበም በእስራኤላዊያን ቀጣሪዎች ዘንድ ብዙም ተፈላጊ እንደማይሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ድርጅቱ አደረግኩት ባለው ዳሰሳ እስራኤላዊያን ቀጣሪዎች ከኢትዮጵያ የሄዱ ያገሩን ዜጎች ከሌሎች ያነሰ ችሎታ አላቸው ብለው ስለሚያምኑ በጽዳት ዘርፍ ለመቅጠር ይፈልጋሉ ብሏል፡፡

በጥናቱ ላይ ሥሟ ያልተጠቀሰ የጥርስ ባለሞያ አገልግሎት ፈልጋ የመጣች ታካሚ ልታክማት ስትል ሌላ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ባለሞያ ያየኛል ብላ መምጣቷን እንደነገገረቻት ሰፍሯል፡፡

የእስራኤል መንግስት ‹ወደ እስራኤል መመለስ› በሚለው ህግ በኢትዮጵያ የሚገኙ በርካታ ፋላሾችን ወደ አገሩ እንደሚወስድ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img