Monday, October 7, 2024
spot_img

ተሰናባቹ የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ለ60 እስረኞች ምህረት አደረጉ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― ተሰናባቹ የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ለ60 ፍርደኛ እስረኞች ምህረት አድርገዋል፡፡

በደቡብዊ የአፍሪካ ክፍል የምትገኘው ዛምቢያ ባሳለፍነው ሳምንት ባካሄደችው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ሂቺሊ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

በዚህ ምርጫ ላይ የተሸነፉት የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ ስልጣናቸውን ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ከማስረከባቸው በፊት በእስር ላይ ላሉ ዜጎች ምህረት ማድረጋቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ የተለያዩ እስር ቤቶች ያሉ ነገር ግን ህመም ያለባቸው፤ በእድሜ የገፉ፤ ሴቶች እና በፖለቲካ ምክንያት ታስረው የነበሩ በድምሩ 60 እስረኞች ምህረት ተደርጎላቸዋል ተብሏል።

ፕሬዝዳንቱ ለእስረኞቹ ምህረት ያደረጉት በዛምቢያ ህገ መንግስት መሰረት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም በፕሬዘዳንቱ ላይ ትችቶችን ይሰነዝሩ የነበሩ እስረኞች በምህረቱ እንዲፈቱ መደረጉ ብዙዎችን አስገርሟል ተብሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img