Sunday, October 6, 2024
spot_img

የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመፍጠር ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ላይ ርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመፍጠር ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ ሰው ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት በሚፈጥሩና የህዝቡን የተረጋጋ ኑሮ ለማወክ ብሎም አገር ለማፍረስ በሚሰሩና በሚተባበሩ ‹‹የህዝብና የአገር ጠላቶች›› ያላቸው ላይ የማያዳግም ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

ይህን ተግባር በበላይነት የሚመራና የሚከታተል በፌዴራል መንግስት እና በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ ግብረሃይል መቋቋሙን የከተማው ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ በዚህ ተግባር ላይ እየተሳተፉ ያሉ ተቋማትና ግለሰቦችን በመጠቆምና በማጋለጥ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img