Monday, November 25, 2024
spot_img

ፍርድ ቤቱ በጌጥዬ ያለው ላይ የአራት ወራት እስር ወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― በትላንትው እለት ነሐሴ 13፣ 2013 ችሎት በመዳፈር ክስ ጥፋተኛ የተባለው ጌጥዬ ያለው ዛሬ ነሐሴ 14 ያስቻለው ችሎት የአራት ወራት እስር እንደበየነበት ጠበቃው ሰለሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡

በጌጥዬ ያለው ላይ ፍርድ ቤቱ የዘጠኝ ወራት እስር ተወስኖ የነበረ ቢሆንም በቅጣት ማቅላያዎቹ የተነሳ ወደ አራት ወራት ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡

እንደ ጠበቃው አቶ ሰለሞን ከሆነ በጌጥዬ ያለው አራት የቅጣት ማቅለያ ያቀረቡ ሲሆን፣ እነዚህም ከዚህ ቀደም የጥፋት ሪከርድ የሌለበት መሆኑ፣ ድርጊቱን መፈፀሙን ማመኑ፣ ድርጊቱን የፈፀመው ከግል ጥቅም ሳይሆን ከፍትሕ ጥማት አንፃር መሆኑንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑ የሚሉ ናቸው፡፡

ጠበቃው ሰለሞን ገዛኸኝ በጌጥዬ ያለው ውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ መናገራቸውን የዘገበው አሻም ቲቪ ነው፡፡

ባልደራስ የተሰኘ የፓርቲ ልሳን አዘጋጅ ነበር የተባለው ጌጥዬ ያለው፣ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት ነሐሴ 4፣ 2013 በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ድረ ገጽ ላይ ‹‹ዋልጌ ዳኞች›› የሚል ጽሑፍ አስነብብቦ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img