Thursday, October 17, 2024
spot_img

ፖሊስ ሕወሓት በዶላር ጥቁር ገበያ በሚያገኘው ገቢ የጦር መሳሪያ ግዥ እንደሚፈጽም ደርሼበታለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 13፣ 2013 ― የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል በሀገር ውስጥና በውጭ ሃገር በተካሄደ ምርመራ እና ክትትል ሕወሓት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የዘረጋውን ሰንሰለት በመጠቀም ዶላርን በጥቁር ገበያ በውድ ዋጋ መሰብሰብ እና የሃዋላ አገልግሎትን መጠቀም በሚያገኘው ገቢ የጦር መሳሪያ ግዥ እንደሚፈጽም ደርሼበታለሁ ሲል አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ባወጣው መግለጫ በዚሁ የሕወሓት ነው ባለው ሰንሰለት በአሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ዱባይ፣ እስራኤል እና በደቡብ አፍሪካ ደርባን፣ ጆሐንስበርግ እንዲሁም ፕሪቶሪ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ናቸው ያላቸውን ግለሰቦች እና ድርጅቶች ሥም ዘርዝሯል፡፡

እንደ ፖሊስ ከሆነ እነዚህ ግለሰቦች ‹‹በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚልኩትን ዶላር አየር በአየር ግብይት በመፈፀም እንዲሁም ዶላሩን እዚያው ውጪ እንዲቀር በማድረግ›› ለሕወሓት ድጋፍ የፋይናንስና የሎጀስቲክ ምንጭ በመሆን እያገለገሉ ስለመሆኑ እወቁት ሲል በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መልእክት ሰዷል፡፡

እነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች እጃቸው እንዳለበት በምርመራ ተረጋግጧል ያለው ፖሊስ፣ ለህግ ለማቅረብ ስም ዝርዝራቸውን ለዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ልኮ በጋራ እየሰራ እንደሚገኝም ነው ያመለከተው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img