Wednesday, October 16, 2024
spot_img

ኦነግ ሸኔ ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያገናኛትን መንገድ ልዘጋ እችላለሁ ማለቱ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 10፣ 2013 ― በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው በመንግስት ኦነግ ሸኔ የሚባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን ኢትዮጵያን እና ኬንያን የሚያገናኘውን መንገድ ልዘጋ እችላለው ሲል ማስጠንቀቁን የኬንያው ኔሽን ጋዜጣ በድረ ገጹ ላይ አስነብቧል፡፡

ጋዜጣው ከቡድኑ ምንጮች አገኘሁ ብሎ ባሰፈረው መረጃ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ በምዕራባዊ ኦሮሚያ በፍጥነት እየገፋሁ እገኛለሁ ማለቱን አስፍሯል።

ቡድኑ የጉጂ ቦረናን ዞን መቆጣጠር እና ወደ አማራ ክልል የሚወስዱትን ቁልፍ መንገዶች መዝጋትን እንደ ወታደራዊ ስትራቴጂ እየተጠቀመ መሆኑን ነው ዘገባው ያሰፈረው።

ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል ዘግቻለሁ ስለሚለው መንገድም ሆነ ዛቻውን በተመለከተ ከመንግስት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት የፈረጃቸው ኦነግ ሸኔ እና ህወሃት ወታደራዊ ጥምረት ማድረጋቸውን ሰሞኑን ማስታወቃቸው ይታወሳል።

መንግስት በበኩሉ ጥምረቱ ብዙ የሚያስገርመው እንዳልሆነ መገልጹም የሚታወስ ነው፡፡
ኬንያን ከኢትዮጵያ የሚያገናኘው የትራንስ አፍሪካ ሀይዌይ ፕሮጀክት አካል የሆነው የ500 ኪሎ ሜትር መንገድ በኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመረቀ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img