Wednesday, October 16, 2024
spot_img

ኡጋንዳ የፓርላማ አባላቷ እንዲከተቡ የሚያስገድድ ህግ አወጣች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 8፣ 2013 ― ኡጋንዳ ህግ አውጪ የፓርላማ አባላቷ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክትባቶችን እንዲከተቡ የሚያስገድድ ህግ አወጣች፡፡

ህጉ ወደ ፓርላማው የሚገቡ የፓርላማው አባላት የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ብቻ መሆን እንዳለባቸው ማስቀመጡን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

እስካሁን ክትባቱን ያልወሰዱ አባላት አሉ ያሉት የፓርላማው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ክሪስ ኦቦሬ “ክትባት ያልወሰዱት እስከ መጪው ማክሰኞ ሊወስዱ ይገባል ካልሆነ ወደ ፓርላማው አይገቡም” ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ህጉ ከፓርላማ አባላቱ በተጨማሪ ጋዜጠኞችን የሚመለከት እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

ወደ ፓርላማው አዳራሽ “ከ100 ሰው በላይ መግባት” እንደማይፈቀድም ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማ 429 አባላት ቢኖሩትም ስብሰባዎቹን በፈረቃ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

በኡጋንዳ ከመጋቢት ወር ወዲህ 1.16 ሚልዮን ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰዳቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img