Sunday, October 6, 2024
spot_img

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀረ ሰላም ባላቸው ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 8፣ 2013 ― የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 8 ጀምሮ ሁሉም የጸጥታ አካላት ‹‹በክልሉ ሽብር ለመፍጠር በሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ኃይሎች›› ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰዱ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹በሃገር ደረጃ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ራሱን ከሰላም ድርድርና ውይይት ያወጣው አሸባሪው የሕወሃት ቡድን ከዚህ ቀደም በሕዝብ ላይ ሲሠራው የነበረው ግፍ ሳይበቃው ዛሬም ድረስ የሃገርን ሕልውና አደጋ ላይ ለመጣል ሴራ ጠንስሶ የቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል፡›› ብሏል፡፡

ቢሮው ሕወሓት ‹‹እጁን በማስረዘም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ዋነኛ የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሲሠራ የቆየው ሳያንስ አሁንም ይህንኑ ተግባሩን በራሱና ያላቻ ጋብቻ ከፈፀሙ ተላላኪ ሌላኛው አሸባሪ የሸኔ ቡድንና ራሱን የጉሙዝ ታጣቂ ነኝ ከሚሉ ኃይሎች ጋር አጠናክሮ›› መቀጠሉን ነው ያስታወቀው፡፡

ከዚህ በኋላ ግን የክልሉ መንግስት እነዚህን ‹‹ጸረ-ሠላም›› ያላቸውን ኃይሎች የሚታገስበት ጊዜ አልቋል ያለ ሲሆን፣ በክልሉ ሽብር ለመፍጠር በሚንቀሳቀሱ ጸረ-ሠላም ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉንም ገልጧል፡፡

በመሆኑም የክልሉ ሁሉም የጸጥታ አካላት የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ በግል የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሁሉ ከዛሬ ነሐሴ 8 ጀምሮ ከሃገር መከላከያ ሠራዊትና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በጸረ-ሠላም ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img