Tuesday, October 15, 2024
spot_img

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ቡድኖች ተኩስ ለማቆም መስማማታቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት የጀመሩትንና የ34 ወታደሮች ህይወት የቀጠፈውን ግጭት ለማቆም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል፡፡

የኤስፒኤልኤም የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ፕዋክ ባልዋንግ በደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የሚመራው ቡድን እና በጀነራል ሲሞን የሚመራው ቡድን ከስምምነት መድረሳቸውን ማስታወቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በሚመራው ኤስፒኤልኤም አይ ኦ ፓርቲ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ክፍፍል ተፈጥሮ ነበር፡፡

በፓርቲው ውስጥ ተፈጥሯል በተባለው ክፍፍልም በሪክ ማቻር የሚመራ እና በጀነራል ሲሞን የሚመሩ ወታደሮች እንዳሉ ይፋ ተደርጓል፡፡

ተኩሱ የተከፈተውም ሪክ ማቻርን የአመራር ክፍትት አለባቸው እንዲሁም በሙስና ተዘፍቀዋል በሚል ከኤስፒኤልኤም አይ ኦ ፓርቲ መሪነት ለማውረድ ሙከራ ከተደረገ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው፡፡

በፓርቲው ውስጥ አፈንጋጭ እንደሆነ የተገለጸው እና በጀነራል ሲሞን የሚመራው ክንፍ ሪክ ማቻር የፓርቲው መሪ አለመሆናቸውን አውጀው ነበር፡፡

ጀነራል ሲሞን፤ ከዚህ በኋላም ሪክ ማቻር ይመሩት የነበረው ኤስፒኤልኤም አይ ኦ ፓርቲ መሪ እኔ ነኝ ማለታቸውን የተገለጸ ሲሆን ለእርሳቸው ታማኝ የሆኑ ኃይሎችም በማቻር ወታደሮች ላይ ተኩስ መክፈታቸው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ለሪክ ማቻር ታማኝ ሆኑት የፓርቲው ቃል አቀባይ ላም ፉል ጋብርኤል በጁባ ከተማ በሰጡት ቃለ ምልልስ በጀነራል ሲሞን የሚመሩ ወታደሮች በካይዛን አካባቢ ተኩስ መክፈታቸውን እንዳረጋገጡለት አል ዐይን ዘግቧል፡፡

ጀነራል ሲሞን የፓርቲው መሪ መሆናቸውን የገለጹት ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በሚዋሰኑበት ሙጋይን አካባቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የደቡብ ሱዳኑ ነጻ አውጭ ንቅናቄ አንጃዎች አመራሮች ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ ከቀናት በፊት ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img