Monday, October 14, 2024
spot_img

በደሴ ከተማ የሰዐት እላፊ ታወጀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 4፣ 2013 ― የደሴ ከተማ አስደዳደር ባወጣው መግለጫ በሰዐት የተገደበ የተሽከርካሪ እና የሰው እንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን አስታውቋል።

ገደቡ የተጣለው ለከተማው ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት መሆኑን አስተዳደሩ ገልጿል።

በዚህም መሠረት ለከተማዋ ነዋሪዎች ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ተከልክሏል።

ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ተቋማትና የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጪ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ እንቅስቃሴ እንዲገደብ ተወስኗል።

የሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 12:00 ብቻ እንዲሆን መወሰኑን የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።

ውሳኔው ከዛሬ ነሀሴ 4፣ 2013 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ያስታወቀ ሲሆን የከተማው ነዋሪዎች ትብብር እንዲያደርጉ የከተማዋ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img