Monday, October 14, 2024
spot_img

ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች በተስፋፋው ጦርነት ሰበብ 300 ሺሕ ሰዎች ረሐብ ተጋርጦባቸዋል ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 4፣ 2013 ― ከትግራይ ክልል ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በመቶ ሺዎች ሰዎች ላይ ረሐብ እንደጋረጠባቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባልደረባ ሚሼል ደንፎልድ በተስፋፋው ጦርነት ሰበብ ረሐብ እንደተጋረጠባቸውና ይህም በአጠቃላይ የተጎጂዎችን ቁጥር ሦስት መቶ ሺሕ እንደሚያደርሰው መግለጻቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል፡፡

በትግራይ ክልል በተመሳሳይ ወደ 400 ሺሕ ሰዎች በጦርነቱ ሰበብ ረሐብ እንደተጋረጠባቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ማሳወቁን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ባለፉት ቀናት የሕወሓት ኃይሎች ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች በመግፋታቸው በርካታ ሺሕ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው መነገሩም ይታወሳል፡፡

የሕወሓት ኃይሎች ባለፉት ቀናት ወደ ፊት ገፍተው የላሊበላን ከተማ መያዛቸው የተነገረ ሲሆን፣ ከትላንት በስትያ ምሽት ደግሞ ወደ ወልዲያ ከተማ የመሣሪያ ጥቃት መሰንዘራቸውን የአማራ ክልል አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img