Friday, October 11, 2024
spot_img

ሕወሃት በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ጦርነት እንደከፈተበት የአፋር ክልል አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 10፣ 2013 ― ሕወሃት በአፋር አርብቶ አደር ሕዝብ ላይ በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ጦርነት መክፈቱን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ አስታውቋል፡፡

ክልሉ ይህ የሕወሃት ተግባር ‹‹በዳር ድንበር አስከባሪው በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ጀግናው የአፋር ሕዝብ›› የከፈተውን ጦርነት ‹‹መንግስት ከሕዝባችን ጋር በመተባበር ይመክታል›› ብሏል፡፡

ክልሉ አክሎም ‹‹ሰላማዊ ክልላችንን ለማተራመስ ሕወሀት የለኮሰው ጦርነት በአጭሩ እንዲገታ አርብቶ አደር ህዝባችንም አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት ማድረግ የሚጠበቅ ሲሆን፣ አካባቢውንም በንቃት ሊጠብቅ›› እንደሚገባ አሳውቋል፡፡

በተጨማሪም ‹‹ሚሊሺያችንና አጠቃላይ የፀጥታ ኃይላችን ይህን በህዝባችን ላይ የተሠነዘረውን ጥቃት የመከላከል ስራ በቁርጠኝነት የሚተገብር ይሆናል›› ብሏል፡፡

የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በመጨረሻም ሕዝቡ ከፀጥታ ሀይሎች ጎን በመቆም በፈንቲ ረሱ ያሎ ወረዳ በኩል የተከፈተውን ጦርነት እንዲመክት እና በክልሉ በየትኛውም አካባቢ ያለው ህዝብ ደግሞ በንቃት አካባቢውን በመቃኘት ከአካባቢው የፀጥታ ሀይል ጋር በትብብር እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img