Monday, October 14, 2024
spot_img

ኢሰመኮ በካማሼ ዞን ምጅንግ ተጠልለው ለሚገኙ ሲቪል ዜጎች ጥበቃ እንዲደረግ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 9፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶቸ ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሐምሌ 3 እና 4፣ 2013 በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በምትገኘው ኢማንጅ ቀበሌ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 16 ሰዎች መገደላቸው መረጃ ደርሶኝ ክትትል ሳደርግ ቆይቻለሁ ብሏል፡፡

ሐምሌ 4፣ 2013 ከአንድ ቀን አስቀድሞ በታጠቁ ኃይሎች ስለመገደላቸው በሚነገር የአንድ የኢማንጅ ቀበሌ ነዋሪ የቀብር ስርዐት ወቅት በተከሰተና የአጸፋ ስለመሆኑ በሚነገር ጥቃት የተጨማሪ 15 ሰዎች ሕይወት ማለፉንም አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ከማሽ ዞን ምንጅጋ ወረዳ ሐምሌ 8፣ 2013 በደንቤ ቀበሌ ሌሎች 8 ነዋሪዎች በታጣቂ ኃይሎች ከተገደሉ በኋላ፣ ስጋት ያደረባቸወ ከአራት ሺሕ ያላነሱ የቀበሌው ነዋሪዎች ተፈናቅለው ምንጅግ ወረዳ ተጠልለው እንንሚገኙም ገልጧል፡፡

እስካካሁን ድረስም በአካባቢው የመሳሪያ ድምጽ እየተሰማ መሆኑን እና የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቦታው ያልደረሱ መሆኑ ተፈናቃዮች ነግረውኛል ሲል አሳውቋል፡፡

ኢሰመኮ ሐምሌ 4፣ 2013 በክልሉ መንግስት እና በኮማንድ ፖስቱ ከተወሰዱ የማረጋጋትና የደህንነት እርምጃዎች በተጨማሪ፣ በምንጅግ ተጠልለው ለሚገኙ ነዋሪዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቋል፡፡

ኮሚሽኑ የክልሉን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለመመለስ አጥፊዎችን በአፋጣኝ ለሕግ ማቅረብ፣ የነዋሪዎችን ሰላም እና ደህንነት በተሟላ መልኩ ማረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነም ነው ያሳሰበው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img