Sunday, October 13, 2024
spot_img

በጎፋ መብራት ኃይል አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያለ አግባብ እንግልት እየደረሰብን ነው ማለታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 3፣ 2013 ― በአዲስ አበባ ጎፋ መብራት ሃይል አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንደተናገሩት በአካባቢው በሚደረጉ ፍተሻዎች በማንነታችን የትግራይ ተወላጆች በመሆናችን እየታሰርን እና ቤቶቻችን እየታሸጉ ነው ሲሉ ቅሬታ ማሰማታቸውን አሐዱ ራድዮ ዘግቧል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንዳሉት ለፍተሻ የሚመጡ የፀጥታ አካላት ምንም አይነት የመፈተሸ ፍቃድ ሳይዙ በተመረጡ የትግራይ ቤቶች ላይ ፍተሻ እያደረጉ ነው።

ቅሬታውን በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ተደጋጋሚ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ገልፀው ስለተፈጠረው ችግር ግን እውቀቱ የለኝም ማለታቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጀላን አብዲም ጉዳዩን እንደማያውቁት ተናግረዋል ነው የተባለው።

እስካሁን አዲስ የወረደ የአሰራር አቅጣጫም ሆነ የቀረበ ቅሬታ የለም፤ ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ችግር አንፃር የተለመደ ሰላም የማሰጠበቅ ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ በሰላም ሚኒስቴር የወንጀል ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ አበራ ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img