Sunday, October 13, 2024
spot_img

በደቡብ ክልል ተመዝብሯል የተባለ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የማስመልስ ተግባር በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 26፣ 2013 ― የክልሉ መንግስት ይህን ያስታወቀው ዛሬ ጠዋት በሐዋሳ ከተማ በተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 12ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የመንግስታቸውን ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ነው።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ርእስቱ ይርዳው በሪፖርታቸው ያቀረቡት ሰነድ በክልሉ በበጀት ዓመቱ በሙስና፣ በታክስ ማጭበርበር እና በውል አስተዳደር 1 ቢሊዮን 439 ሚሊዮን 635 ሺሕ 699 ብር ተመዝብሯል ብሏል።

የተመዘበረውን የሕዝብ ሀብት በክልሉ ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ አማካኝነት የማስመለስ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ያለው የምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ሪፖርት፣ ‹‹እስከአሁንም ከተመዘበረው 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ውስጥ ከክስ በፊት በተካሄዱ ድርድሮች እና በፍርድ ውሳኔዎች ከ389 ሚሊየን ብር በላይ ለማስመለስ ትችሏል፡፡ ቀሪውን ገንዘብ ለማስመለስ በክስ ቀጠሮ እና በፍርድ አፈጻጸም ሂደት ላይ እንገኛለን›› በማለት አብራርቷል።

ሪፖርቱ በክልሉ ተካሂዷል ያለው ምዝበራ በየትኞቹ ተቋማትና በእነማን እንደተፈመ ግን የጠቀሰው ነገር አለመኖሩን የዘገበው ዶይቸ ቬለ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img