Wednesday, November 27, 2024
spot_img

የጓንታናሞ የስቃይ አለቃ ነበሩ የሚባሉት የቀድሞ የአሜሪካ ባለሥልጣን ሞቱ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 25፣ 2013 ― የቀድሞው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ዶናልድ ረምስፊልድ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋለል፡፡ የአገሪቱን የመከላከያ ሚኒስቴር በጆርጅ ደብሊው ቡሽ ዘመን የመሩት ረምስፊልድ፣ አሜሪካ በኢራቅ ላይ ያደረገችውን ወረራ የመሩ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ረምስፊልድ በአፍጋኒስታን፣ በኢራቅ እና በጓንታናሞ የተደረጉ የማሰቃያት ተግባራት ላይ ትእዛዝ ሰጪ ሰው ነበሩ፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጠበቆች በተደጋጋሚ ዶናልድ ረምስፊልድን በጦር ወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ተደጋጋሚ ጥረቶችን ቢያደርጉም፣ አለመሳካቱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በሌላ መረጃ በፀረ ታሊባን እና አልቃዒዳ ዘመቻዎች ሰበብ 20 ዓመታትን በአፍጋኒስታን ያሳለፈው የአሜሪካ ጦር ለቆ ወጥቷል፡፡

በቁጥር እስከ 3 ሺሕ 500 ይደርሳሉ የተባለላቸው የጦሩ ወታደሮች፣ ዛሬ ከካቡል በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የባግራም አየር ማዘዣ ጣቢያን ለቀው ወጥተዋል፡፡

የጦሩ መውጣት አሜሪካ በአፍጋኒስታን የነበራት ወታደራዊ ተልዕኮ ለመጠናቀቁ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም፤ ምናልባትም ከታሰበው በፊት ሊፈጥን እንደሚችል ቢጠበቅም እንኳን፤ ጦሩ ተጠቃሎ ሙሉ በሙሉ ከአፍጋኒስታን የሚወጣው እስከ መስከረም 11 ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img