Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢብራሂም ሬሲ የኢራንን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 12፣ 2013 ― ኢራናዊያን በትላንትናው ዕለት ባካሄዱት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የቀድሞው ዳኛ ኢብራሂም ሬሲ ምርጫው ማሸነፋቸው ተነግሯል፡፡

እኚህ ተመራጭ ፕሬዘዳንት አሜሪካ በሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት ማዕቀብ ከጣለቸባቸው ኢራናዊያን መካከል አንዱ ናቸው ነው የተባለው፡፡ ተሰናባቹ የኢራን ፕሬዘዳንት ሐሰን ሮሃኒን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት ለኢብራሂም ሬሲ እንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን በማድረስ ላይ መሆናቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

የምርጫው ውጤት ቆጠራው እስካሁን በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ዳኛ ኢብራሂም ሬሲ ከወዲሁ ፕሬዘዳንት የሚያደርጋቸውን ድምጽ ማግኘታቸው ታውቋል። በኢራን በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተሳተፉት መራጮች ጋር ሲነጻጸር 44 በመቶ አንሶ መገኘቱም ተነግሯል፡፡

ለአስራ ሦስተኛው ጊዜ በተካሄደው ባለው የኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አራት እጩዎች ተወዳድረዋል።

በዚህ ውስጥ ሦስቱ ከአክራሪ ክንፍ ሲሆኑ፣ አንድ እጩ ደግሞ ለዘብተኛና የመካከል ፖለቲካ የሚራምድ የለውጥ አራማጆች የሚደገፍ ነው፡፡

የኢራን የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን ካለው የመራጮች ተሳትፎ ማነስ የተነሳ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በመጀመርያ ዙር የምርጫ ሂደት ላያልቅ ይችላል የሚል ግምት አስቀምጠው ነበር።

በዚህ ምርጫ ሶስቱን አክራሪ ክንፍ የወከሉት ኢብራሂም ረኢሲ፣ ሙህሲን ሪዳኢ እና አሚር ሂሴን ሲሆኑ፣ አብዱልናስር ደግሞ ለዘብተኛና የመካከል ፖለቲካ ክንፉን ወክለዋል፡፡

በኢራን ምርጫ ህግ መሠረት የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ የሚሆነውና መንበረ ስለጣኑን የሚቆናጠጠው ሙሉ ድምጽ ያገኘ ተመራጭ ሲሆን፣ እጩዎቹ በመጀመሪያው ዙር የሚጠበቅባቸውን ድምፅ ካላገኙ ግን ብዙ ድመፅ ያገኙ እጩዎች በሁለተኛው ዙር ይወዳደራሉ መባሉን የዘገበው አል ዓይን ሚዲያ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img