አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 3፣ 2013 ― በክልሉ በግጭት ሳቢያ 9 ሺሕ አባወራዎች ወይም 55 ሺሕ 163 ሰዎች መፈናቀላቸውን የምሥራቅ ወለጋ ዞን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በክልሉ ለተፈናቃዮቹ ቁጥር ማሻቀብ በቅርቡ የምሥራቅ ወለጋ ዞኖች በሆኑት በሊሙ እና ሐሮ ሊሙ ወረዳዎች እንዲሁም በቤንሻጉል ጉሙዝ ከማሼ ዞን ያሶ እና ሶጌ ወረዳዎች የነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ነው መባሉን አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል፡፡
በተለይ በወለጋ ዞኖች የታጠቁ ኃይሎች መኖራቸው የጸጥታ ሁኔታውን ተለዋዋጭ ማድረጉንና ይህም የሰዎች መፈናቀል እና ሕይወት መጥፋት ማስከተሉን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ መግለጹንም ዘገባው አስታውሷል፡፡
በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖችም ጥቂት ቀናት የቀሩትን ምርጫ በማስመልከት በሦስት እግር ተሸከርካሮች ላይ የሰአት እላፊ ገደብ እንደተጣለም ተነግሯል፡፡