Thursday, October 10, 2024
spot_img

በካናዳ በጥላቻ በተነሳሳ ጥቃት የአንድ ሙስሊም ቤተሰብ አባላት ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 1፣ 2013 ― በካናዳ በአንድ የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰብ ላይ ባነጣጠረ ጥቃት አራት አባላት በመኪና ተገጭተው መገደላቸው ተነግሯል፡፡ ቤተሰቡ የተገደለው ሆን ብሎ በተቀነባበረ ጥቃት እንደሆነ ፖሊስ አጋልጧል።

በኦንታሪዮ ግዛት በተፈጸመው ጥቃት የቤተሰቡ አንደኛው ልጅ ብቻ ሲተርፍ፣ ይኸው ከጥቃቱ ተራፊ የዘጠኝ ዓመቱ ታዳጊ በሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለትም ይገኛል፡፡

በዚህ ጥቃት የ74 እና 44 ዓመት ሁለት ሴቶች፣ አንድ የ46 ዓመት ወንድ እንዲሁም የ15 ዓመት ታዳጊ ሕይወታቸው ተቀጥፏል፡፡ 

ይህን የተቀነባበረ ግድያ በመፈፀም ናትናኤል ቬልትማን የተባለ የ20 ዓመት እድሜ ያለው ካናዳዊ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በአራት ሰዎች ግድያ ወንጀልና በታዳጊው ደግሞ በግድያ ሙከራ ክስ ቀርቦበታል።

ይህ ግለሰብ ከገደላቸው የቤተሰብ አባላት ጋር ምንም አይነት ትውውቅ እንደሌለው ቢነገርም፣ በወቅቱ ግን የጥይት መከላከያ ጃኬት አድርጎ እንደነበር ፖሊስ ገልጧል፡፡

‹‹ቤተሰቡ ሙስሊሞች ስለሆኑ ነው የተገደሉት ብለን እናምናለን›› ያለው ፖሊስ፣ ይህ በጥላቻ ተነሳስቶ የተፈፀመ ግድያ ከመሆኑ አንፃር ግለሰቡን በሽብር ለመጠየቅ ፖሊስ እየመረመርኩ እገኛለሁ ብሏል፡፡

ግድያው በርካቶችን ያስደነገጠና ማሳዘኑ ሲነገር፣ በሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ግድያና በማይነገር ጥላቻ የተሞላ ነው በማለትም የግዛቲቱ ከንቲባ ኤድ ሆልደር ግድያውን አውግዘውታል።

ከንቲባው በግዛቲቱ ለሦስት ቀናት ያህልም የሐዘን ቀን በማስመልከት ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አዘዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img