አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 27፣ 2013 ― የጤና ሚኒስቴር ለውጭ ተጓዦች የሚሰጠውን እና የሚቀበለውን ከኮሮና ወረርሽኝ ነጻ መሆን የሚያሳይ ምስክር ወረቀት ወደ ዲጂታል መቀየሩን አስታውቋል፡፡
ምስክር ወረቀቱ ዲጅታል እንዲሆን የተደረገው የወረቀት ምስክር ወረቀቱ በተጭበረበረ መንገድ እየተሰራ እንደሆነ ስለተደረሰበት ነው፡፡
በመሆኑም ከኢትዮጵያ የሚወጡ ወይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ሌሎች መዳረሻዎች የሚሸጋገሩ ተጓዦች ከቀጣዩ ሰኞ ጀምሮ ዲጅታል ምስክር ወረቀት እንዲያቀርቡ የጤና ሚንስትሯ ሊያ ታደሠ በጻፉት ደብዳቤ ማዘዛቸውን ፎርቹን ዘግቧል፡፡