አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 24፣ 2013 ― የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አገሪቱን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እና በጥብቅ ሲፈለጉ ነበሩ ያላቸውን የሕወሃት አባላት በጅቡቲ መንግሥት በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ መግባታቸውን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል በሰሜን ዕዝ ላይ እና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሰው ወደ ጎረቤት ሀገር ሸሽተው ተይዘዋል ያላቸው ሀብቶም ገብረስላሴ ወልዩ፣ መሰለ ታመነ እሼቱ እና ኮለኔል መሐመድ በሪሁ ኑር የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡
በቁጥጥር ስር የዋሉትን የሕወሃት አባላት በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተጠርጣሪዎችን ተረክቦ ጉዳዩን በህግ አግባብ የሚያጣራ መሆኑን የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡