Sunday, November 24, 2024
spot_img

‹‹የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት›› እጄ ገብተዋል ያላቸው ሦስት ቻይናዊያን መለቀቃቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 21፣ 2013 ― ራሱን ‹‹የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት›› ብሎ የሚጠራውና በመንግሥት ‹‹ኦነግ ሸኔ›› የሚባለው ቡድን ከግንቦት 7፣ 2013 አንስቶ በቁጥጥሬ ስር ይገኛሉ ያላቸው ሦስት የቻይና ዜጎች መለቀቃቸው ተነግሯል፡፡

በምዕራብ ወለለጋ መንዲ አካባቢ ታግተው ነበር የተባሉት የተባሉት ሁዋግ፣ ሂ እና ዋንግ የተሰኙ ቻይናዊያን፣ በታጣቂ ቡድኑ መለቀቃቸውን እንዲሁም ለዓለም ዐቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ተወካይ ማስረከቡንም ቡድኑ ማሳወቁን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ተይዘው ነበር የተባሉትን እነዚህን ቻይናውያን በተመለከተ በወቅቱ አስተያየጥ የሰጡት የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኤልያስ ኡመታ በታጣቂዎች ታግተዋል መባሉን ‹‹ሐሰት ነው›› ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር፡፡

እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራው ቡድን በወቅቱ ባወጣው መግለጫ በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ አቅራቢያ የተያዙት ሦስቱ የቻይና ዜጋ የሆኑ የማዕድን ሠራተኞች መሆናቸው አመልክቶ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img