Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ሰበር ዜና እነ ጃዋር መሐመድ ከዛሬ ጀምሮ ፍርድ ቤት መቅረብ አንፈልግም አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ 24 ተከሳሾች ከዛሬ ጀምሮ ጉዳያቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ አስታወቁ። ተከሳሾቹ በትግራይ እየተካሄደ ነው ያሉትን ‹‹የጅምላ ግድያ እና ኢ ፍትሐዊ አገዛዝ›› ለመቃወም ለሁለት ቀናት የረሃብ አድማ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ያለመቅረብ ውሳኔያቸውን ያስታወቁት፤ መደበኛ የክስ ሂደታቸውን እየተመለከተ ላለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ የፀረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ በጽሑፍ ባቀረቡት አቤቱታ ነው። በችሎቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ጃዋር መሐመድ የኮሎኔል ገመቹ አያና እና የሌሎች ተከሳሶችን ጉዳይ በመጥቀስ የፍርድ ቤት ውሳኔ በተገቢው መንገድ ተፈጻሚ እየሆነ አይደለም ብለዋል።

‹‹እኛ እዚህ የመጣነው ከተፈረደብን ለመቀጣት፤ ነጻ ከተባልን ለመውጣት ነው›› ያሉት አቶ ጃዋር፤ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ በገዛ ፍቃዳችን ፍርድ ቤት አንቀርብም›› ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በትግራይ ክልል እየተከሰተ ላለው ሁኔታ የትግራይ ህዝብ የረሃብ አድማ ላይ በመሆኑ፤ እነርሱም ለሁለት ቀናት ምግብ እንደማይበሉም አቶ ጃዋር አክለዋል። የረሃብ አድማው በትግራይ ክልል በትግራይ ክልል እየተካሄደ ነው ያሉትን “የጅምላ ግድያና ኢ-ፍትሃዊ አገዛዝ ለመቃወም” መሆኑን ማስረዳታቸውን የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img