Monday, November 25, 2024
spot_img

በመራዊ ብልጽግና ፓርቲን ለመደገፍ የተጠራ ሰልፍ ለሰው ሕይወት መጥፋት ሰበብ ሆነ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 13፣ 2013 ― በትላንትናው እለት በመራዊ ከተማ ብልጽግና ፓርቲን ለመደገፍ ሰልፍ በወጡ ሰዎችና በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የሰው ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል፡፡

የመራዊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች አነሳስተውታል በተባለው አመጽ 1 ፖሊስ እና 8 ተማሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው፣ የአንድ ተማሪ ሕይወት አልፏል የተባለ ሲሆን፣ በርካታ ተማሪዎችም ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

አዲስ ዘይቤ የተባለ ድረ ገጽ እንደዘገበው በአካባቢው የተፈጠረው አለመግባባት መነሻ ብልጽግና ፓርቲን የሚደግፈው ሰልፍ በመካሄድ ላይ እያለ በቅጥር ግቢያቸው ውስጥ የሚገኙት የመራዊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ውጥረት በመፍጠራቸው ነው፡፡

ተማሪዎቹ ከግቢ ለመውጣት በሚያደርጉት ሙከራም ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው የተነገረ ሲሆን፣ ከተማሪዎቹ በተወረወረ ድንጋይ አንድ ፖሊስ ሲጎዳ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት የአንድ ተማሪ ሕይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ ተማሪዎቹ ከግቢ ለመውጣት በሚደረግ ግፊያ በርካታ ተማሪዎች ለቀላል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የመራዊ ከተማ ፖሊስ ኢንስፔክተር ምትኬ መነሻ ምክንያቱ ገና እንዳልተጣራ የተናገሩ ሲሆን፣ ሰልፍ መካሄዱንና ተማሪዎቹም ተቃውሞ መሰማታቸውን ግን አረጋግጠዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img