Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከትላንት በስቲያ ምሽት በተነሰዘረ ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን፤ አቤ ዶንጎሮ ወረዳ ወለጌ ቀበሌ ላይ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ምሽት ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ‹‹ሙሉ ለሙሉ›› ቀያቸውን ለቅቀው መሰደዳቸውን የዓይን እማኞች ነግረውኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

በዚሁ ጥቃት ከተገደሉት ሶስት ሰዎች ውጭ አራት ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የዞኑ አስተዳዳሪ የጥቃቱ መፈጸምን እና የሶስት ሰዎችን መገደል ቢያረጋግጡም፤ ነዋሪዎች ሙሉ ለሙሉ አልተፈናቀሉም ሲሉ አስተባብለዋል።

በወለጌ ቀበሌ “አዲስ አለም” በሚል መጠሪያ ከምትታወቀው አካባቢ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ታጣቂዎቹ በአካባቢያቸው ላይ ተኩስ የከፈቱት ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ ነው።

በጥቃቱም ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች ሲገደሉ ስድስቱ ደግሞ መቁሰላቸውን አስረድተዋል። በአቤ ዶንጎሮ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የነበሩ የዓይን እማኝ፤ በጥቃቱ የተጎዱ አምስት ሰዎችን በህክምና ቦታው ተመልክቼያለሁ ማለታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img