አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― ከመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጫንጮ ቀበሌ ወደ ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ላይ የነበሩት ተመስገን ገነቲ እና ኤልያስ አሳዬ የተባሉ ሁለት ተማሪዎች ላይ በአማራ ክልል ቻግኒ ከተማ የክልሉ ታጣቂዎች ምሽት ላይ ማረፊያ ክፍላቸው ድረስ በመዝለቅ ጥቃት እንዳደረሱባቸው ተሰማቷል፡፡
ታጣቂዎቹ በወሰዱት ጥቃት ተመስገን ገነቲ የተባለው ተማሪ ክፉኛ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቷል የተባለ ሲሆን፣ ሌላኛው ተማሪ ኤልያስ አሳዬ እስካሁን የደረሰበት እንዳልታወቀ ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
በአካባቢው በዚህ ሳምንት መጨረሻ ተመሳሳይ ድርጊት ተፈጽሞ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ መንግሥት የወሰደው እርምጃ ስለመኖሩም የተሰማ ነገር የለም፡፡