Monday, October 7, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነጻ ሕክምና እንዲሰጥ ወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 27፣ 2013 ― የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች በከተማዋ አስተዳደር ስር ባሉ የጤና ተቋማት በሙሉ ነጻ ሕክምና እንዲሰጥ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ 80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ከነጻ ሕክምና አገልግሎቱም በተጨማሪ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የጠየቀው መሬት እንዲሰጠው መወሰኑንም ምክትል ከንቲባዋ አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ነው፡፡

በየዓመቱ ሚያዝያ 27 ቀን የሚከበረው የአርበኞች ቀን በዓል ፋሺስት ጣሊያን በመስከረም 1928 በወልወል በኩል የጀመረው ወረራ አጠናክራ ለአምስት ዓመታት አገሪቱ በወረራ ከያዘችበት በኢትዮጵያውያን ተጋድሎና አርበኛነት በድል የተጠናቀቀበት ነው፡፡

የወቅቱ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከቆዩበት የእንግሊዟ ባዝ ከተማ በሱዳን በኩል በምዕራብ ኢትዮጵያ ኦሜድላ ላይ ጥር 12 ቀን 1933 የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ያውለበለቡበት ከወራት ቆይታ በኋላም ከአርበኞች ጋር የዘለቁበትና በዕለተ ቀኑ ሚያዝያ 27 አዲስ አበባ የደረሱበት ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img