Monday, October 7, 2024
spot_img

የትግራዩ ግጭት 5 ሺሕ ሕፃናትን ከወላጆቻቸው ለይቷል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― በትግራዩ ግጭት ምክንያት ወደ 5 ሺሕ የሚጠጉ ሕጻናት ከወላጆቻቸው ጋር ተለያይተዋል ያለው የሕጻናት አድን ድርጅት ወይም ሴቭ ዘ ችልድረን ነው፡፡

ሕጻናት አድን ድርጅቱ እንዳለው ከወላጆቻቸው የተለዩት እነዚህ ሕፃናት በአሁኑ ወቅት በስደተኛ እና ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።

ከወላጆቻቸው የተለዩት ሕፃናት ለረሃብ፣ ለአካላዊ እና ጾታዊ ጥቃቶች ተጋላጭ ናቸው ያለው ድርጅቱ፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ለበርካታ የክልሉ ሥፍራዎች እርዳታ ማቅረብ ባለመቻላቸውም ሕፃናቱ ያለማንም ድጋፍ እራሳቸውን ለመርዳት ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጧል፡፡

ከስድስት ወራት በላይ ባስቆጠረው የትግራይ ጦርነት ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ቀያቸውን ጥለው መሰደዳቸው የሚነገር ሲሆን፣ ይኸው ጦርነት በክልሉ የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ እንዳያስከትል በሚል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሲያስጠነቅቅ ይሰማል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ሕፃናት፣ የሚያጠቡ እና ነብሰ ጡር እናቶች ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት እያጋጠማቸው ስለመሆኑም የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ እያለ ይገኛል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img