Monday, October 7, 2024
spot_img

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አበረ አዳሙ መሞታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― ባለፈው ሳምንት ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርነት ሥልጣናቸው ተነስተው በሌላ የተተኩት አበረ አዳሙ በዛሬው እለት ነው መሞታቸው የተሰማው።

ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ዛሬ ጠዋት ባልታወቀና በድንገት ማረፋቸው ታውቋል።

በጉዳዩ ላይ ከክልሉ መንግሥትም ሆነ ከቤተሰቦቻቸው እስካሁን የተሰማ ነገር የለም።

ላለፉት ሁለት ዓመታት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ባለፈው ሳምንት ቦታቸው በአዲስ ሰው መተካቱ በክልሉ ሚዲያ ቢዘገብም እርሳቸው ስለመነሳታቸው ግን በክልሉ መንግሥት በይፋ አልተነገረም ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img