Sunday, September 22, 2024
spot_img

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የጠ/ሚ ዐቢይ ተቺ የሆኑትን ግለሰብ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪያቸው አድርገው ሾሙ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 16 2014 ― ከቀናት በፊት የተካሄደውን የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድ፤ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተቺ የሆኑትን ሑሴን ሸይኽ ዓሊን የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪያቸው አድርገው ሾመዋል፡፡

በደኅንነት ጉዳዮበደኅንነት ጉዳዮች ላይ የካበተ ልምድ አላቸው የሚባሉት ሑሴን ሸይኽ ዓሊ ሹመት የተሰማው አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድ ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ፎርማጆ ጋር የሥልጣን ርክክብ አድርገው ቪላ ሶማሊያ ወደተሰኘው የአገሪቱ ቤተ መንግሥት መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሽፋን ባገኘው የሥልጣን ርክክብ፤ የሶማሊያ ሕዝብ ተወካዮች እና የታችኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም የጦር ኃይሎች አባላት ተገኝተዋል፡፡

በሥልጣን ርክክቡ ወቅት ፋርማጆ ሶማሊያዊያን ከአዲሱ ፕሬዝዳንት ጋር በትብብር መንፈሥ እንዲሠሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ አዲሱ ፕሬዝዳንትም የቀደሙትን ፎርማጆን ለአገራቸው ለሰጡት አገልግሎት በማመሥገን በሥልጣን ቆይታቸው ለሶማሊያ ጥቅም እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድ የሥልጣን ርክክር ማድረጋቸውን ተከትሎ ሑሴን ሸይኽ ዓሊን የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪያቸው አድርገው ከመሾማቸው በተጨማሪ፣ ለፕሬዝዳንቱን ጽሕፈት ቤት በተመሳሳይ አዳዲስ አለቃዎችን መርጠዋል፡፡  

ከሶማሊያ ጋር በተገናኘ ሌላ መረጃ የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት መሐመድ ፎርማጆ በኤርትራ 5 ሺህ ሶማሊያዊያን ምልምል የወታደር ሠልጣኞች አምና ሥልጠናቸውን እንዳጠናቀቁ ለመጀመሪያ ጊዜ መግለጻቸው ተነግሯል፡፡

ፎርማጆ በሶማሊያ ከዓመት በላይ ያወዛገበውን የሠልጣኞቹን ፋይል ትላንት በተካሄደው ሥነ ሥርዐት ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሸይክ ማሕሙድ አስረክበዋል። አዲሱ ፕሬዝዳንትም ሠልጣኞቹን በቶሎ ወደ አገራቸው ለመመለስ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

ሰልጣኞቹ አምና ያልተመለሱት የሶማሊያ ምርጫ እስኪጠናቀቅ መሆኑን ፎርማጆ ተናግረዋል ተብሏል። የእነዚህ ሠልጣኞች ጉዳይ ባለፈው ዓመት ቤተሰቦቻቸውን ወደ ሞቃዲሾ አደባባዮች ለተቃውሞ ሠልፍ ያስወጣ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img