Sunday, November 24, 2024
spot_img

ለጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 30 2014 ― የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው።

ዛሬ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ውጊያ ለመሩ፣ ሀይል ለመሩ፣ ድልና ውጤት ላስገኙ ከፍተኛ የጦሩ መኮንኖች በየደረጃው የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት 1 የፊልድ ማርሻል ማዕረግ፣ 4 የሙሉ ጀነራል ማዕረግ፣ 14 የሌተናል ጀነራል ማዕረግ፣ 24 የሜጀር ጀነራል ማዕረግ እና 58 የብርጋዴር ጀነራል ማዕረግ ተሰጥቷል።

የጀነራል መኮንኖቹ ሹመት በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አቅራቢነት በርዕሰ ብሄሩ ፕሬዚደንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ነው የተሰጠው።

ሽልማቱን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጠው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ለጦር መሪዎች የተሰጠው ማዕረግ እና የተሸለሙት ሜዳልያ በመጀመሪያ ደረጃ በጦር ሜዳ ውሏቸው የፈጸሙትን ጀብዱ ታሳቢ ያደረገ ነው ብሏል።

የሽልማቱ ሁለተኛ ምክንያት ቀብድ ነው ነው ያለው መግለጫው፣ ለጦር መሪዎቹ ‹‹ጀግንነታችሁ ተቋማዊ ቅርጽ እንዲይዝ፤ ትጋታችሁ ከግለሰባዊ እሴትነት አልፎ የሠራዊቱም እሴት እንዲሆን ከዛሬ ጀምሮ በርትታችሁ መሥራት አለባችሁ›› የሚል መልእክት ሰዷል፡፡  

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img