Monday, October 7, 2024
spot_img

ዐብደላ ሐምዶክ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ለቀቁ

  • አሜሪካ ለአገሪቱ መሪዎች ማሳሰቢያ ሰዳለች

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 25 2014 ― የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን አሳውቀዋል፡፡ ሐምዶክ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጠናቸውን መልቃቸውን ያሳወቁት በቴሌቪዥን በተላለፈ የቀጥታ ሥርጭት ነው፡፡

ዐብደላ ሐምዶክ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የአገሪቱን የረዥም ዐመታት መሪ ዑመር አልበሽርን ካስወገደው መፈንቅለ መንግስት በኋላ ነበር፡፡

ሐምዶክ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ በሀገሪቱ ጦር በመሪ ሌተናል ጀነራል ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን መሪነት በተፈጸመ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ተነስተው በቁም እስር ላይ የቆዩ ሲሆን፣ ከጦሩ ጋር በተደረገ ፖለቲካዊ ስምምነት ወደ ስልጣናቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

ሆኖም ወደ ሥልጣናቸው ከተመለሱ ከሳምንታት በኋላ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በሱዳን ባለፉት ቀናት የሀገሪቱ አስተዳደር ወደ ሲሺል እንዲመለስ የሚጠይቁ ሰልፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በቅርቡ በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች በጸጥታ ሃይሎች የተገደሉትን ለማሰብ እና ጥቅምት ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ለመጠየቅ ነው፡፡

ከቀናት በፊት ተካሂዶ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በኦምዱርማን ከተማ ብቻ ስድስት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸው ሪፖርት ተደርጓል፡፡ የሱዳን ሐኪሞች ማህበር በሀገሪቱ ተቃውሞ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ50 መብለጡን ገልጿል።

የዐብደላ ሐምዶክን ሥልጣን መልቀቅ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ የሚገኝ ሲሆን፣ የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ፣ የሱዳን መሪዎች ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው መግባባት ላይ እንዲደርሱና የሲቪል አስተዳደሩ ስልጣን መቀጠሉን ማረገገጥ እንደሚገባ አሳስባለች፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቀጣዩ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስቱን መሠረት ባደረገ መልኩ እንዲሾም ብላለች፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img