Friday, November 22, 2024
spot_img

በዋግኽምራ ታጣቂዎች 11 ሰዎችን መግደላቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 20፣ 2013 ― በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በኒሯቅ ከተማ ከትላንት በስትያ ታጣቂዎች ጥቃት ከፍተው 11 ንፁህ ነዋሪዎችን ሲገድሉ በንብረት ላይ ውድመት ማድረሳቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ሰኞ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተኩል ሲሆን ደርሷል የተባለውን ጥቃት ዶይቸ ቨሌ ከአካባቢው ነዋሪዎችም አረጋግጫለሁ ብሎ ዘግቧል፡፡

የዋግኽምራ ብሔረሰብ የአማራ ክልል ሚሊሺያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ ጥቃቱ ‹‹ጁንታ›› ብለው በጠሯቸው ኃይሎች መድረሱን በመግለጽ፣ በአጠቃላይ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጠና መሆኑን አስረድተዋል፡፡

እነዚህ ታጣቂዎች ከወር በፊት በዞኑ ፃግብጂ ወረዳ ፃታ በተባለች ከተማ ተመሳሳይ ጥቃት አድርሰው የሠዎች ሕይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ የሚታወስ ነው፡፡

የአማራ ክልል ባለሥልጣናት የታጠቁ ኃይሎች ክልሉን የግጭትና የትርምስ ማዕከል ለማድረግ በሁሉም አቅጣጫዎች ሙከራ እያደረጉ እንደሆነ በተለያዩ ጊዜ በሰጧቸው መግለጫዎች ሲናገሩ መሰንበታቸውንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img