Saturday, May 18, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ጋር በምታደርገው ድርድር የተፈጠሩ ልዩነቶች አለመፈታታቸው ተነገረ


አምባ ዲጂታል፤ ቅዳሜ ሚያዝያ 12፣ 2016 – ኢትዮጵያ ከዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ)ን ድጋፍ ለማግኘት በምታደርገው ድርድር አሁንም ልዩነቶች እንዳሉ የዘገበው ሬውተርስ የዜና ወኪል ነው፡፡

የዜና ወኪሉ የአይኤምኤፍ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ አበዳሪው የገንዘብ ተቋም ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር እያካሄደ ባለው ውይይት ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ቢጠበቅም ልዩነቶች ግን አልተፈቱም። ድርድሩ በቀጣይ እንደሚቀጥል ያመለከተው ዘገባው፣ አገሪቱ የገንዘብን የመግዛት አቅም እንድታዳክም ልትገደድ እንደምትችል ጠቁሟል። ይህ ገንዘብን የሚዳከም ውሳኔ በአይኤምኤፍ ሰዎች በግልጽ ባይጠይቅም፣ የሚለቀቀው ብድር ያንን ማድረግ የሚጠይቅ ነው፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እያመነቱ የቆዩበትን ብርን ከዶላር ምንዛሬ አንጻር የማዳከም ውሳኔ ምናልባትም ካቀዱት ጊዜ ቀድመው ሊያላልፉ እንደሚችሉ ከዚህ ቀደም ተዘግቦ ነበር።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት አንድ የአሜሪካን ዶላር በመደበኛ ምንዛሬ በ56.70 ይሸጣል፡፡ በአንጻሩ በትይዩ (በተለምዶ አጠራር ጥቁር ገበያ) ከ117 እስከ 120 ብር ይሸጣል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የገንዘብ ተቋማትን ብር የማዳከም ጥያቄ ተቀብላ ውሳኔ ካሳለፈች ባለፉት ዓመታት ለኢኮኖሚው ፈተና ሆኗል የሚባለውን የዋጋ ግሽበት እንደሚያባብሰው ባለሞያዎች ሲያስጠነቅቁ ይደመጣል፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም ገንዘብ ድርጅት የጠየቀችው የገንዘብ ድጋፍ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img